የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ መማር ማስተማር እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር ባዘጋጀው የሰላማዊ መማር ማስተማር እቅድ ላይ የዩኒቨርሲቲው  አመራሮች፣መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሟልተው በተገኙበት ውይይት አካሂዷል፡፡በውይይቱም የሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት እና ተቋማት  የሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታ ፣አሁን እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችና ወደፊት  ችግሮችን ለማስተካካል ምን እየተሰራ እንደሆነና  ከባለድረሻ አካላት የሚጠበቁ ተግባራትን በዝርዝር የያዘ የማወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል ፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ታምሬ ዘውዴ የመወያያ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የ2011 ዓ.ም የመማር ማስተማር ስራን በርካታ ውጣውረዶችን በጋራ አልፈን ያለምንም  የፀጥታ ችግር  የአመቱ  የትምህርት ስራ መጠናቀቁን  በስኬት አውስተው የነበረውን ጠንካራ ተግባር አዳብረን በማቀጠል የ2012ዓ.ምን  የትም/ዘመን ፍጹም ሰላማዊ እንድሆን ሁሉም በሀላፊነት መንፈስ የየድርሻውን መስራት እንደሚያስፈልግ በአፅንኦት ተናግረዋል ፡፡

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ም/ፕሬዝደንት የሆኑት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ እንደተናገሩት ተቀራርቦ በመነጋገር፣ በመግባባት፣በሰለጠነ አኳኋን ለችግሮች መፍትሄ የመስጠት ባህልን በመገንባትና  የዩኒቭርሲቲውን ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች በጋራ በማለፍ ዩኒቨርሲቲው ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ   የተቋቋመለትን አላማ እንድሳካ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ፡፡

                                                መስከረም 18/2012 5��;P=����

Leave a Reply

Your email address will not be published.