የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመካነሰላም ካምፓስ የላም እርባታና የበሬ ማደለብ ስራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

Info Research news


የካቲት 15/2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
አቶ ታደለ ሙሴ በዩኒቨርሲቲው የገቢ ልማትና ሀብት ማመንጫ ቡድን መሪ እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲውን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ በሁለቱም ካምፓሶች የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ቱሉ አውሊያ ካምፓስ የላም እርባታን ጨምሮ በግ የማርባትና ማደለብ ስራዎች በመስራት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ መሆኑን አስታውሰው በተመሳሳይ በመካነ ሰላም ካምፓስም የላም እርባታና የበሬ ማደለብ ስራ ለመጀመር የቤት ግንባታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.