የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሰላማዊ መማር ማስተማር ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ

Latest News

2012 ዓ.ም የትምህርት አመት ውጤታማ እንድሆን በሰላማዊ መማር ማስተማር ርዕሰ ጉዳይ ላይ   የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣የወረዳ አመራሮች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች ና የፀጥታ  ሃይሎች በተገኙበት  በሁለቱም ግቢዎቹ መስከረም 23 እና 24 ውይይት አካሂዷል፡፡በውይይቱም ላይ  ባለፈው  2011 ዓ.ም  ሰላማዊ መማር ማስተማርን ከማስፈን አኳያ ከላይ የተጠቀሱ አካለት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው የተገለፀ ሲሆን ምንም እንኳን የጎላ የጸጥታ ችግር ባይከሰትም አልፎ አልፎ ሲያጋጥሙ የነበሩ  መጥፎ አዝማሚያዎች  የበለጠ  መሰራት  እንዳለበት የሚጠቁም መሆኑም ተነስቷል፡፡

ዶክተር ካሳሁን አህመድ የጥናት ምርምር ና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት በ2012 ዓ.ም ሰላማዊ መማር ማስተማርን ለማካሄድ፣ጥናትና ምርምር ለማድረግ እንድሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት ሁለት ነገሮች አስፈላጊ ናቸው ያሉ ሲሆን አንደኛው የውስጥና የውጩን ማህበረሰብ በማስተባበር ወደ ልማት ማስገበት ሁለተኛው የተቋቋመው የትምህርት ተቋማት ሰላማዊ መማር ማስተማር  ጥምር ኮሚቴ ስኬታማ እንድሆን  የጋራ እርብርብ ማድረግ  ናቸው ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲተው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘውደ በበኩላቸው እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ባብዛኛው በዩኒቨርሲቲው ግንባታ መጓተት ምክኒያት የተፈጠሩ  በመሆናቸው በያዝነው አመት ጊዜያዊ አጥር  በመገንባት ዩኒቨርሲቲው የሁሉም በመሆኑ ሁሉም ያቅሙን በመስራት ግቢያችንን ውብና ሰላሙ የተጠበቀ እንድሆን በጋራ እንስራ ሲሉ  ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ አመራርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል የሆኑት አቶ እጅጉ መልኬ የህብረተሰቡን ተዋዶና ተፋቅሮ በጋራ አብሮ የመኖር ባህል እንደ መልካም አካጣሚ በመጠቀም፣ የሚያግጠሙ ችግሮችን  ተነጋግሮ በመፍታት፣ከሁሉም በላይ ህግና ስርዓት  እንድከበር በመስራት   ዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ የትምህርት እና  የምርምር ተቋም   ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

                                             መስከረም 25/201

Leave a Reply

Your email address will not be published.