የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በክረምት ወራት መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ሰጠ ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲው  በክረምቱ  ወራት መርሃ ግብር  በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ዙሪያ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ለተማሪዎች፣መምህራንና የሴክተር መሰሪያ ቤት ሰራተኞች በአጠቃላይ ለ261 ያህል ሰልጣኞች በተከታታይ 4 ዙር ስልጠና እንድወሰወዱ ተደርጓል፡፡

የስጠናው አላማም ዩኒቨርሲቲው በሚሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት የአካባቢው ተማሪዎች፣መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች መሰረታዊ የኮምፒዩተር አጠቃቀም ክህሎት እንድኖራቸው መድረግ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው  አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳ ሻወል ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦችም  computer basics ,  the internet,cloud services and world wide web, productivity programmes,computer security and privacy, digital life style በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡

በእቅድ ደረጃ ስልጠናው በቱሉ አውሊያና መካነሰላም በሚገኙት ሁለቱም  ካምፓሶች ከ500 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች እንድሳተፉበት  ታቅዶ እየተሰራ እና በመካነሰላም ካምፓስ ስልጠናው ገና ያልተጠናቀቀ መሆኑን የህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ወንድማገኝ አሰፋ አስውቀዋል፡፡

  ከአሰልጣኞቹ መካከል አቶ ያሲን አረጋ እንደገለጹት  አብዛኛው ሰው የኮምፒዩተር አጠቃቀም ክህሎት የሌለው በመሆኑ  ስልጠናው በሰፊው ቢሰጥ  መልካም ነው ብለዋል፡፡

የቱሉአውሊያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የሂሳብ ሰራተኛ የሆኑት የስልጠናው ተሳታፊ ቀሲስ አለሙ በላይ ከስልጠናው ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኙበትና  ስራቸውንም የሚያቀላጥፍላቸው መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

                                              ነሀሴ 13/2011 hem�3�^�/

Leave a Reply

Your email address will not be published.