የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር ደም ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  በደቡብ ወሎ ውስጥ ከሚገኙ 10 የምዕራብ ወረዳዎች እና ከደቡብ ወሎ ዞን ከተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በጥቁር ደም ዙሪያ  ከ2-3/2011 የምክክር መድረክ አካሒዷል፡፡በምክክር መድረኩ ላይም  አመራሮች፣የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች  የተገኙ ሲሆን በአጠቃላይ 152 ሰዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒሰቴር ባለሙያ የሆኑት አቶ እንድሪያስ ወዳጆ እና አቶ ማስረሻ አበበ ስለጥቁር ደም ምንነት ፣መንስኤና መከላከያ ዘደዎቹ ጥናታዊ ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት ጥቁር ደም የመገዳደልና የመበቃቀል  መጥፎ ባህል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ እሸቱ የሱፍ እንደተናገሩት ጥቁር ደም ወይም ደም የመመለስ ኋላ ቀር አስሳሰብ በዞናችን ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ቀውስ እያስከተለ በመሆኑ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ወደፊትም  በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የማስረፅ ተግባሩ ቢቀጥል መልካም መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ወንድየ አድማሱ  በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት በበኩላቸው እንደገለፁት ይህን  የምክክር ፕሮግራም  ለማዘጋጀት መነሻችን ከወረዳዎች በመጣ ጥያቄና የችግሩን ስፋት ከመገንዘብ መሆኑን አስረድተው በቀጣይም በዚህ  አሳሳቢ ጉዳይ ዙሪያ ሰፊውን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ይቀጥላል ብለዋል፡፡ 

በመጨረሻም የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች የጥቁር ደምን አስተሳሰብና ድርጊት የሚያወግዝና የመፍትሄ አቅጣጫን  የሚያሳይ  ባለ5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል፡፡(ግንቦት 5/2011) x

Leave a Reply

Your email address will not be published.