የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በጥናትምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በምርምር ፕሮፖዛል ላይ የውስጥ ግምገማ አካሄደ

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትምርምርናማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንትጽ/ቤት በጥናትምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮፖዛል ላይ  ከህዳር 13 /2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት  በሁለቱም ግቢዎች  የውስጥ ግምገማ  አካሂዷል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የጥናት ምርምርና ማህበርሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት ጽ/ቤት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የአካባቢውን ችግር መሰረት ያደረጉና ችግር ሊቀርፍ የሚችሉ በግብርና ኮሌጅ  አስራ ሶስት(13) ፣በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ሰባት(7)፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚስ ኮሌጅ አስራ ሶስት(13)፣ በማህበራዊ ስይንስ ኮሌጅ አራት(4) ፣ጠቅላላ  ሰላሳ ሰባት(37) የምርምር ፕሮፖዛል የቀረበ ሲሆን በማህበሰብ አገልግሎት ዘርፍ  ደግሞ  በግብርና ኮሌጅ  ስምት (8) ፣በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ አስራሶስት(13)፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚስ ኮሌጅ  አስር (10) ፣በማህበራዊ ስይንስ ኮሌጅ አስር (10) ጠቅላላ  አርባ አንድ (41) የፕሮፖዛል ሰነዶች ተገምግመዋል፡፡ በተጨማሪም  ከቴክኖሎጂ ሽግግር አንፃር በግብርና ኮሌጅ ሶስት (3) ፣በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ አንድ ( 1)  በድምሩ አራት (4) ፕሮፖዛሎች  ቀርበው ተገምግመዋል፡፡

በግምገማው ወቅትም 146 የዩኒቨርሲቲው መምህራን የተሳተፉ  ሲሆን የመከነሰላም ግቢ ጀኔራል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሽበሽ  አለባቸውም መምህራንን  ግንባር ቀደም በመሆን ለማነሳሳት ያዘጋጁትን የጥናታዊ ጽሁፍ ፕሮፖዛል  ለግምገማው በማቅረብ የአካባቢውን ችግር በጥናት ለመፍታት ያላቸውን ፍላጉት አሳይተዋል ፡፡ከላይ የቀረቡት 82 ፕሮፖዛሎች ቅድሚያ በድፓርትሜንትና በኮሌጅ ደረጃ ተገምገመው ያለፉ ሲሆን  አሁን በዩኒቨረሲቲ ደረጃ  በጋራ የተገመገሙ ናቸው ፡፡ በቀጣይም በሀገር ደረጃ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ  ሙህራንን በመጋበዝ ተገምግመው የሚያልፉና ወደተግባር የሚለወጡ መሆኑን የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ካስሁን አህመድ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት  ዝግጅት ክፍል መረጃውን አድርሰውናል፡፡    

Leave a Reply

Your email address will not be published.