የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም አድስ የተመደቡ ተማሪዎችን ተቀበለ

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  በ2012 ዓ.ም በሁለቱም ካምፓሶች ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍል አድስ የተመደቡ 2500 ተማሪዎችን የቅበላ ኮሚቴ በማዘጋጀት ጥቅምት 11እና 12  ተቀብሏል፡፡

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉአውሊያ ካምፓስ ያገኘናት ከአዳማ የመጣችው ተማሪ ሰናይት ታደሰ አቀባበሉን በተመለከተ በሰጠችው አስተያየት አቀባበሉ ደስ የሚልና እንደቤተሰብ እንድሰማን ያደረገ ነው፤አየሩም ቀዝቃዛ ነው የሚባለው የሚወራውን ያህል ሳይሆን የሚለመድ ነው ብላለች፡፡

ከቡኖ በደሌ ወረዳ  ልጃቸውን ይዘው የመጡት አባት አቶ ሰለሞን ተፈራ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ለተማሪዎች ከተደረገው ጥሩ አቀባበል በተጨማሪ  ወላጅ እንዳይገባ ሳይከለከል የልጆቻችንን ሁኔታ በደንብ  እንድናይ ስለተደረገ እናመሰግናለን  ያየነው መልካም ነገር  እንድቀጥል  አደራ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው  አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻወል  ለዩኒቨርሲተው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቀደም ሲል  እንደገለፁት  ባለፉት  አመታት  የምንታወቅበትን ሰላማዊ ሁኔታ  በማጠናከር  ተማሪዎች ያለምንም ችግር ውጤታማ ሆነው እንድመረቁ  በማድረግ የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ ለማሳካት ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

                      ጥቅምት 13/2012  �n<���C

Leave a Reply

Your email address will not be published.