የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከለጋምቦ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለአገልግሎት ሰጭተቋማት ባለቤቶች ስልጠናሰጠ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ  ዩኒቨርሲቲ  ከለጋምቦ  ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአገልግሎት አሰጣጥ፣በሳኒቴሽንና ታክስ ዙሪያከሚያዚያ 24-25 ለ35አገልግሎትሰጭተቋማትባለቤቶች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን  የሰጡት  በወሎ ዩኒቨርሲቲ  የማርኬቲንግ ማኔጅመንት  መምህር  የሆኑት አቶ ደሳለኝ ተስፋው  ሲሆኑ የስልጠናው ዋና  አላማ   የንግዱ ማህበረሰብ  ያሉበትን ያገልግሎት አሰጣጥ  ክፍተቶች ለመሙላት  ጥሩ የንግድ ክህሎትን በማስረፅ ተገልጋዩ እየረካ  እነሱም ውጤታማ  የሚሆኑበትን ሁኔታ  ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

አቶ ደሳለኝ ተስፋው  ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት በዘልማድ የሚሰሩ ንግዶች ጊዜያዊ ጥቅም እንጅ  ዘለቄታዊ አዋጭነትናቀጣይነት  ስለማይኖራቸው  ዘመኑን የተከተለ የንግድ አሰራርን መከተል  አስፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በመቅደላ አምባ  ዩኒቨርሲቲየማህበረሰብ  አገልግሎት ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር  የሆኑት አቶ ወንድማገኝ አሰፋ  እንደተናገሩት  የማህበረሰቡን  ችግር ማቃለል አንዱ የዩኒቨርሲቲው ዋና ተግባር በመሆኑ  እየታየ ያለውን ያገልግሎት አሰጣጥ ችግር  ለመፍታት  ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያ በመጋበዝ   ስልጠናው እንድሰጥ አድርገናል ብለዋል፡፡የስልጠናው ተሳታፊዎች  በበኩላቸው ስልጠናው  አስፈላጊና ጥሩ ግንዛቤ ያገኙበት  እንደነበር  ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም  አሰልጣኝ አቶ ደሳለኝ  ተስፋው  እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ሲለወጥ  አካባቢውም  አብሮ መለወጥ ስላለበት በቀጣይም ሰፋ ያለ የንግዱን ማህበረሰብ ባካተተና ለውጥ ሊያመጣ በሚችል መልኩ  ስልጠናዎችን ማዘጋጀት ቢቻል ጥሩ ነውሲሉ  መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ (ሚያዚያ25/2011) <�?�”�3

Leave a Reply

Your email address will not be published.