የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረጡ 10 ወረዳዎች ለመጡ አመራሮች በጥናትና ምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

Latest News Research news

ዩኒቨርሲቲው በጥናትና ምርመር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸውየምዕራብ ወሎ 10 ወረዳዎች ለጋምቦ፣ተንታ፣ቦረና፣መቅደላ፣ወግዲ፣ከለላ፣ለገሂዳ፣መሃል ሳይንት፣ሳይንት አጅባርና ጃማ ሲሆኑ የስልጠናው አላማም ዩኒቨርሲቲውእየሰራቸው ስለሚገኙና ሊያከናውናቸውስላቀዳቸውስራዎች ግንዛቤ የመፍጠር፣ከተሳታፊዎች ግአቶችን የመውሰድ እና ወደፊት ሊሰሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ስምምነት ላይ መድረስ መሆኑ በስልጠናው ወቅት ተገልዋል፡፡

ዶ/ር ወንድየ አድማሱ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት  ም/ፕሬዝዳንት  ለተሳታፊዎች እንዳሰረዱት ምዕራብ ወሎ  የተፈጥሮ እምቅ ሀብት ያለው  በመሆኑ ተቀናጅተን በጋራ በመስራት  አካባቢውን በከፍተኛ ደረጃ መለወጥ ይቻላል ብለዋል፡፡

አቶ አንዷለም በላይ የጥናትና ምርምር  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው  በጥናትና ምርምር ስራችን አሁን ባለን አቅም 6 ፕሮጀክቶችን ሰርተን 2ቱ  ወደ ተግባር የተገባባቸው ናቸው ብለዋል፡፡በዚህም የመጀመሪያው እና ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው  ችግኝ ጣቢያ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ  ለማቋቋም 2.3 ሔክታር መሬት ተወስዶ  ካሣ ተበጅቶለት  ስራው የተጀመረ ሲሆን  በሁለተኛ ደረጃ ሊሰራ የታቀደው  በተመረጡ 4 ወረዳወች  ውስጥ ለሚገኙ 400 ገበሬዎች ከስልጠና ጀምሮ ልዩልዩ ድጋፎችን  በማድረግ በአትክልትና ፍራፍሬ  ልማት እንድሰማሩ በማድረግ ተጠቃሚ እየሆኑ ሲመጡ ወደሌሎች የማስፋፋት ስራ እንደሚከናወን ተገልፀዋል፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ  አቶ ወንድማገኝ አሰፋም ስለማህበረሰብ  አገልገሎት ምንነት፣ የትኩረት አቅጣጫዎቹና ባለፈው አመት በማህበረሰብ አገልግሎትስለተሰሩ ስራዎችና ወደፊት ሊሰሩ ስለታሰቡ  ጉዳዮች ገለፃ አድርገዋል፡፡

መበጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች  በነበራቸው ቆይታ መደሰታቸውንና ለአካባቢያችን ለውጥ በጋራ  ለመስራት  ከዩኒቨርሰቲው  ጎን እንቆማለን  ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.