የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር የጋራ የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲዉ የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመዉ ከደሴ ቲሹ ካልቸር ሴንተር ፤ከወ/ሮ ሲህን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፤ከደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያና ከደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሠነድ ህዳር 15/03/2013 ዓ/ም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘዉዴ ጋር ተፈራርመዋል፡፡በጋራ የመስራት ዋና አላማዉ ዩኒቨርሲቲዉ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮዉን ለመወጣት በቴክኖሎጅ ሽግግር ፤በላብራቶሪ ምርምር የታገዘ ስራ ለመስራት ፤ሀገር በቀል እዉቀቶችንና ባህልና ቅርስን ለመጠበቅ እንድሁም ስራ አጥነትን ለመቀነስ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ነዉ ሲሉ የዩኒቨርሲቲዉ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ አስረድተዋል፡፡የደሴ ቲሹ ካልቸር ሴንተር ስራ አስኪያጅ አቶ ሀሰን እንድሪስ በስምምነት ፊርማው ወቅት እንደገለፁት በተቋማችን ዩኒቨርሲቲዉ ጋር አብረን የምንሰራቸዉሶስት መስረታዊ ተግባሮ ያሉ ሲሆን እነሱም በላብራሪ የታገዘ ምርምር መስራት ፤ቴክኖሎጅወችን የመለዋወጥ ስራ ለመስራት እና ተማሪዎችን በተግባር የታገዘ ትምህርት እንዳገኙ በማድረግ አብረዉ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ሌሎችም እንድሰሩ ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር አብረዉ ለመስራት ቃል በመግባት ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.