የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ለባለ ድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲዉ ከደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝ መምሪያ ፣ ከምዕራብ ወሎ 11 ወረዳዎች ከተዉጣጡ የወረዳ አስተዳዳሪወች ፤የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፤የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ከህዳር 15-16/3/2013ዓ/ም ለ2 ተከታታይ ቀናት ስልጠናዉ ተሰጥቷል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ልምድ ባላቸዉ ባለሙዎች ባህልና ሀገር በቀል እዉቀቶች ፣የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ፤ተፈጥሮዊና ሰዉ ሰራሽ ቅርሶች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጥተል፡፡በስልጠናው ወቅት ሰልጣጮች በየወረዳቸው ያለውን ባህል ፣ሀገር በቀል እውቀት እንድሁም ቅርስ ጠብቆ ለትወልድ ከማስተላለፍ አንጻር ያለባቸውን ክፍተት እንደሙሞላ እና ጉል አስተዋጾ እንዳለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፡፡የዩኒቨርሲቲዉ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ ዩኒቨረሲቲያችን ትኩረት ሰጥቶ ግንዛቤ የተፈጠረበት ዋና አላማ በምዕራብ ወሎ ውስጥ ብዙ ታሪካዊ ሰውሳራሽና ተፈጥሮዊ ሀብቶች ፤የሀገርበቀል እውቀቶችን በመጠበቅ ለምርመር ስራ እንድውሉ በማድረግ ለትውልድ የማሻገር ስራ ለመስራት ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ ስለይማን እሸቱ በስልጠናዉ ማጠቃለያ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና በዞናችን ምዕራባዊ ወረዳወች ባሉ ባለ ድርሻ አካላት መስጠቱ ዕምቅ የሆነ የባህልና ቅርስ ባለቤት የሆነዉን ዞናችንን ሀብቱን ጠብቆና ተንከባክቦ ለትውልድ ለማሻገር ጉልህ አስተዋጾ እንዳለው ተናግረው ስልተናው ተጠናቋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.