የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በምርምሩ ዘርፍ ለተሰማሩ መምህራን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ ልምድ ባላቸው አንጋፋ ምሁራን በምርምሩ ዘርፍ ለተሰማሩ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪ መምህራን በምርምርና ማህበረስብ አገልግሎት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና (Training for Enhancing the knowledge and skills of University Research and Community services practitioners ) በሁለቱም ግቢዎቹ ለተከታታይ 8 ቀናት እየተሰጠ ይገኛል ፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ የካዳሚክ ጥናትና ምርምር ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አብዱሮህማን አወል እንደገልጹት ስልጠናው በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን በምርምሩ ዘርፍ ለተሰማሩ የግቢያችን መምህራን የአካባቢውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ያገኙ ዘንድ ከአጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር መሰጠቱ ለተመራማሪዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር አሰረድተዋል፡፡ስለጠናውን በመስጠት እየተሳተፉ ያነጋገርናቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ገናነው አግተው በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ለመምህራን ያደረገው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በጋራ የመሰራት ፣የልምድ ፣የእውቀት ና ተባብሮ ለመስራት አቅም የሚፈጥር በመሆኑ መምራህራንም ልምድ ለማገኘት ያላቸው ፍላጎትም የሚያስደስት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.