የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ስልጠና ሰጠ

Latest News Research news

ዩኒቨርሲቲው  በሁለቱም ካምፓስ ለሚገኙ  ከ700 በላይ ለሚሆኑ የካፌና የፅዳት ሰራተኞች  የሃይጅንና ሳኒቴሽን   ስልጠና ሰጥቷል ፡፡  ፡፡

የስጠናው አላማም ዩኒቨርሲቲው በሚሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት ተቋሙ የማህበረሰቡ ማህበረሰቡ የተቋሙ በሚል  መሪ ቃል  ግልጋሎቱን ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለመጀመር በማሰብ የዩኒቨርሲቲውን  ና የአካባቢውን  ማህበረሰብ  ጤና አጠባበቅ ለማሻሻል መሆኑን   የጥናት  ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት  ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ  ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦችም   የምግብ ንጽህና፣የውሃ ንጽህና፣የኣካባቢ ንፅህና ፣የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እንድሁም የተማሪዎችና ሰራተኞች ጤና አጠባበቅ  በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡትና የወሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አቶ ሚስጥር ልንገረውና አወቀ ካሴ ስልጠናው የንፅህናና ጤና አጠባበቅ ስርዓታችንን በማሻሻል የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ  ጤና ለመጠበቅና ጥሩ ስም እንድኖረው በማድረግ የዩኒቨርሲቲውን ገፅታ ለመገንባት ይጠቅማል  ብለዋል፡፡

ከአሰልጣኞቹ መካከል  አንዳንዶች  እንደተናገሩት  ስልጠናው የነበረንን የጤና አጠባበቅ እውቀት  በማሳደግ ለተሻለ ስራ  የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡

                               ጥቅምት 12/2012 ��>�/%C

Leave a Reply

Your email address will not be published.