የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የአስ/ ሰራተኞች ሸማቾች ህብረት ስራ ማህብር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የአስ/ ሰራተኞች ሸማቾች ህብረት ስራ ማህብር 3ኛ ዙር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ መስከረም 26/2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ የጉባኤው ዋና ዋና አጀንዳዎችም የማህበሩን አመታዊ ኦድት ምርመራ በአባላቱ ማፀደቅ፣የ2014 ዓ.ም አመታዊ የማህበሩን እቅድ ማፀደቅ፣የተጓደሉ ኮሚቴዎችን ማሟላት እና ተጨማሪ እጣ ሽያጭ መወሰን የሚሉ ናቸው፡፡ማህበሩ በአሁኑ ሰዓት 282 አባላት ያሉት ሲሆን በዘመኑ ሂሳብ ምርመራ 139 ሺ 286 ብር ያተረፈ መሆኑ በኦድት ተረጋግጠዋል፡፡የበጀት እጥረት፣የገበያ ውጣ ውረድ፣በቂ የካፌ ግብአት ከህጋዊ ነጋደዎች አለማግኘት እንድሁም ዘይትና ስኳር ለአባላት አለማዳረስ የሚሉት ማህበሩን ያጋጠሙት ችግሮች ተብለው የተለዩ ናቸው፡፡በሌላ በኩል በምርመራ ወቅት ጉድለት ያለመገኘቱ፣ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ የካፌ አገልግሎት መሰጠቱ፣የሂሳብ አያያዝ ስርዓቱን ጠብቆ መሰራቱ፣ትርፍ ክፍፍል መደረጉና አባላት ተጨማሪ እጣ እንድገዙ መደረጉ የሚሉት በጥናካሬ የታዩ ናቸው፡፡ማህበሩ በቀጣይ አመታዊ ትርፉን ወደ 282ሺ ብር ለማድረስ መታቀዱ የተገለፀ ሲሆን ማህበሩን በበጀት ለማጠናከርም ተጨማሪ እጣ ሺያጭ የማከናወንና ብድር የማመቻቸት ስራ የሚከናውን መሆኑ ተገልጸዋል፡፡

መስከረም 26/2014 ዓ.ም

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦ website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.