የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለሁለት ተከታታይ ቀናት የ2013 እቅድ ን በጥንካሬና በድክመት በመለየት የአመቱን የስራ አፈጻጸም በመገምገም የ2014 እቅድ ኦረንቴሽን ላይ በመወያየት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው አመራር የስነ-ምግባርናየፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት እንድቋቋም ከማድረግም አልፎ የሰው ሃይል እንዲመደብለት በማድረግ በስነ-ምግበርና በሙስና ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ ስልጠና /ግንዛቤ/ እንድሰጥ ማገዙ፣አሰራ ስድስት/16/የብልሹ አሰራር ጥቆማዎችን በመቀበል እና በማጣራት እርምት እንድወሰድ መድረጉ፣በአመቱ ውስጥ የቀረቡ 11 ቅሬታዎች መልስ የተሰጣቸው መሆኑ ፣በዩኒቨርሲቲዉ ሀብት ማስመዝገብ ያለባቸዉ ሰራተኞች መረጃ ልየታ መደረጉ ፣የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ክበብን በማደራጀት ለዳይሬክቶሬቱ አጋዥ እንድሆን መደረጉ፣የመስክ ምልከታ በማድረግ ችግሮች ቀድመዉ እንድፈቱ ማድረጉ፣:የልምድ ልዉዉጥ በማድረግ የእዉቀት፣የክህሎት እና የአመለካከት ችግሮችን መፍታት መቻሉ እንድሁም ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት መፍትሄ እንድያገኙ መደረግ መቻሉ የሚሉት በአመቱ የተሻሉ ዋና ዋና አፈፃፀሞች ተብለው የተወሰዱ ናቸው፡፡በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው አድስ እንደመሆኑ የፌደራልስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በቦታው ተገኝቶ ያደረገው ድጋፍ አናሳ መሆን ፣ቅሬታ ቀርቦባቸው ምላሽ እንድሰጡ የሚጠየቁ ክፍሎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን፣ተገቢ መረጃ በወቅቱ አለመስጠት፣ዳይሬክቶሬቱ ማወቅ ያለበትን አዳዲስ አሰራር ለማሳወቅ አልፎ አልፎ ጅምሩ ቢኖርም በተጠናከረ ሁኔታ ስልጠና አለማግኘት፣በተቋሙ ውስጥ ሊፈፀም የሚችል ሙስናን የመከታተል ኃላፊነት የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ብቻ አድርጎ ማየት እንድሁም የተቋማት ኃላፊዎች ስለ ተቋማዊ የ ተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆንና ለመተግበር ቁርጠኝነት ማነስ የሚሉት ደግሞ የነበሩ ክፍተቶች ተብለው በዋናነት የተለዩ ናቸው፡፡ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ማከናወን፣የብልሹ አሰራር መከላከል ስራን ማከናወን፣ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ጥናት በማድረግና በመለየት መፍታት፣የሀብት ምዝገባና እድሳት ስራን ማጠናከር፣የሙስና ከመላከል ከውስልን በበቂ ሁኔታ ወደ ስራ ማስገባት እንድሁም አለም አቀፍ የፀረሙስና ቀንን በድምቀት ማክበር የሚሉት የቀጣይ ዋና ዋና የስራ አቅጣጫዎች ውስጥ መሆናቸውም ተገልፀዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የስነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ፈንታው ባሰተላለፉት መልዕክትም ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች ብትሆንም ባለው ውስብስብ የሌብነት መረብ የተነሳ ሙስና የሀገሪቱ የእድገት ማነቆ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው አሁን መንግስት ለፀረ -ሙስና ትግሉ ልዩ ትኩረት የሰጠ በመሆኑ በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
