የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል እውቀት ማስተባበሪያ የማህበረሰቡን ባህልና ቅርስ ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት አድረጎ እንደሚሰራ ገለፀ።

Latest News

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል እውቀት አስተባባሪ የሆኑት መምህር አብርሃም በቀለ እንደተናገሩት ማህበረሰቡ ያሉትን ባህሎችና ቅርሶች ባግባበቡ እንድይዝና እንድንከባከባቸው ቅድሚያ ያሉትን ሀብቶች ሊያውቃቸው የሚገባ በመሆኑ ቅርሶችን ማስተዋወቅ ላይ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ይህንንም አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችል ዘንድ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የሀገርህን እወቅ ክበብ በማቋቋም ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡የሀገርህን እወቅ ክበብ መመስረቻ ውይይት ላይ የተገኙት የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ሰውአገኝ አስራት (ዶ/ር) እንደተናገሩትም ቅርሶችንና ባህሎችን ለማወቅ፣ለማጥናትና ለመጠበቅ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በሁለንተናዊ መልኩ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.