የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መረጃ አሰተዳደር ስልጠና ሰጠ

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተማሪዎች መረጃ  አሰተዳደር   /student information management system/SIMS/ ሶፍትዌር ስልጠና  ለዩኒቨርሲቲው አካ/ጉ/ም/ፐሬዝዳንት ስር  ላሉ  ሁሉም ዳይሬክተሮች ፣ኮሌጅ ዲኞች ፣የትምህር ክፍል ሃላፊዎች እና ኳሊቲ ኮርድኔተሮች ለአንድ ሳምንት ያክል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን ወ/ሪት ማሪያና ተስፋየ እንደገለፁት ይህ ሶፍትዌር  ስልጠና መሰጠቱ የውስጥ አሰራራችንን ለማዘመን ና ተከታታይነት ያለው መረጃ በመያዝ ቀልጣፋ፣ጊዜና ወጭ ቆጣቢ አሰራርን ለመዘርጋት ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

 የዩኒቨርሲቲው የአይሲቲ  ዳይሬክተር አቶ ሙሉ ቀን ታሪኩ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከ345ሺህ  ብር በላይ  የሰርቨር ግዥ በመፈጸም /student information management system/SIMS ሶፍትዌር ለዩኒቨርሲቲያችን አገልግሎት እንድሰጥ ማደረጉ የተማሪዎች መረጃ ማዘመን ብቻ ሳይሆን የሰው ሃይል መረጃና የዶርሚታሪ መረጃ አያያዝ ስረአት ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው  ገልፀዋል፡፡  

በባህርዳር  ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌሩ  ባለቤት ከሆኑት አንዱና ስልጠናውን የሰጡት መምህር አሰፋ  እንደገለፁት መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አድስ እንደመሆኑ  ከወድሁ መረጃውን በሲስተም ውስጥ ማስገባት መጀመሩ ዩኒቨርሲቲው ለሲስተም የሰጠው ግምት እጅግ የሚደነቅና የተሻለ አሰራርን የሚከተል መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

                     ሀምሌ 25/2011 �=�U�G

Leave a Reply

Your email address will not be published.