የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ክፍል የተደራሽነት አድማሱን እያሰፋ ነው፡፡

Latest News

የተከታታይ ትምህርት ክፍሉ በ2011 የትምህርት ዘመን በክረምት፣ በቅዳሜና እሁድ ከጀመራቸው የትምህርት ዘርፎች በተጨማሪ በ2014 የትምህርት ዘመን የተደራሽነቱን በማስፋት በቱሉ አውልያ ዋናው ግቢ ፣በመካነሰላም ካምፓስ፣በአቀስታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በገነቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በማታ እንድሁም በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር በድግሪ ፕሮግራም እንድሁም በደቨሎፐመንት ኢኮኖሚክስ፣በእንግሊዘኛ ቋንቋ /TEFL/ እና እንስሳት እርባታ /animal production/ በቱሉ አውልያና መካነሰላም ግቢዎች በሁለተኛ ድግሪ /ማስተርስ/ ፕሮግራም በጥቅሉ በ22 ድፓርትመንቶች ለማስተማር ትምህርት ፈላጊዎችን እየመዘገበ ይገኛል፡፡ተደራሽነቱንም ለማስፋት በደሴና ደብረብርሃን ኤፍ ኤሞች በጥምረት፣ በደቡብ ወሎ ምዕራባዊ ወረዳዎችን በተለያዩ የመገናኛ ዘድዎች የቅስቀሳ ሰራ ተሰርቷል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ክፍል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ወሰኑ ታደሰ እንደተናገሩት ፕሮግራሞቹ ዩኒቨርሲቲው በሙያው የሰለጠኑ መምህራንን በተገቢው ለመጠቀምና የአካባቢውን ማህበረሰብ በትምህርት ተጠቃሚ ለማድረግ በማለም በማኔጅመንት ተነጋግሮ በእስታንዳርዱ መሰረት እንድከፈቱ የተወሰነ ስለሆነ ማህበረሰቡ የተፈጠረውን እድል በመጠቀም ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ይገባዋል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.