የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአማካሪ ምክር ቤት የሰላም ፎረም አካሄደ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ በላቀ ደረጃ ለመወጣት ያስችለው ዘንድ የአካባቢውን ማህበረሰብ በንቃት በማሳተፍ የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢን ለመፈጠር የሚያስችል የአማካሪ ምክር ቤት ቀደም በሎ ማቋቋሙ የሚታወሰ ሲሆን በአሁን ሰዓት በዋናው ግቢ ቱላውሊያ ካምፓስ የአማካሪ ምክር ቤቱን የሰላም ፎረም አካሂዷል፡፡የአማካሪ ምክር ቤት ፎረም ያሰፈለገበት አላማም ተቋሙ ካለበት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ሰላምን ለማምጣት፣ የማህበራዊ አገልግሎቶችን በቅርበት ለማግኘት፣ችግሮች እንዳይፈጠሩ ለመከላከልና ሲፈጠሩ በዘላቂነት ለመፍታት መሆኑ ተገልፀዋል፡፡ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ የሰላም ፎረሙን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት “አሁን ያለንበት ወቅት 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ትንሽ ቀናት የቀሩበት፣የአባይን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ለማከናዎን የተዘጋጀንበትና ግብፅና ሱዳን የውስጥ የጥፋት ሃይሎችን በመጠቀም ትርምስ ለመፍጠር የተዘጋጁበት አስቸጋሪ ጊዜ ላይ የምንገኝ በመሆኑ የአማካሪ ም/ቤት አባላትና የአባባቢው መስተዳድር አካላት ከወትሮው በተለየ መልኩ ተማሪዎቻችንን የምንመክርበትና የአካባቢውን ማህበረሰብ የምናነቃበት እንድሁም እቅዶቻችንን የምናሳካበት ሰዓት ላይ የምንገኝ መሆኑን በመገንዘብ ከዛሬው ግምገማ ማግስት በተደራጀ መልኩ በጊዜ የለኝም መንፈስ እንድሰራ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ“በማለት መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡የደቡብ ወሎ ዞን የዋና አስተዳዳሪ፣ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢና የዩኒቨርሲቲው የአማካሪ ምክር ቤት ፎረም ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሰይድ መሃመድ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ወሎ ሰው መሆን በቂ ነው በሚል እሴቱ ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበት ምድር በሆኑ ይህ መልካም እሴት እንዳይሸረሸርና ሰላማችን እንዳይደፈርስ ሁሉም ነቅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ግንቦት 25/2013

Leave a Reply

Your email address will not be published.