የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአማካሪ ምክር ቤት ፎረም በዋናው ግቢ ቱሉ አውልያ ካምፓስ አቋቋመ፡፡

Latest News

የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በላቀ ደረጃ እንድወጡ የአካባቢውን ማህበረሰብ በንቃት በማሳተፍ የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢን ለመፈጠር የሚያስችል የአማካሪ ምክር ቤት በዋናው ግቢ ቱላውሊያ ካምፓስ አቋቁሟል ፡፡ የአማካሪ ምክር ቤት ፎረም አባላት የሚያካትታቸው የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የአስተዳደር ደህንነት እና ፀጥታ ዘረፍ ሃላፊዎች፣የተንታ ወረዳ እና የለጋምቦ ወረዳ የሁሉም የሀይማኖት አባት ተወካዮች፣ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎቸና የአስተዳደር ፀጥታ ሃላፊዎች፣ተቋሙ ያለበት ውሃና ፍሳሽ ቢሮ ሃላፊ፣የለጋንቦ ወረዳ ኤሌክትሪክ አገልግሎተ ሃላፊ፣ተቋሙ ያለበት ወረዳ የቴሌኮም አገልግሎት ሃላፊ፣ታዋቂ ያገር ሸማግሌዎቸ፣ታዋቂ ግለሰቦቸ እንድሁም የአካባቢ ወጣቶቸ ተወካዮቸ ያካተተ ምክር ቤት መሆኑ ተገልጸዋል፡፡ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ ምክር ቤቱን ሲያቋቁሙ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በላከው የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአማካሪ ምክር ቤት የአሰራር ማዕቀፍን በዝርዝር በማስረዳት የፎረሙ አባላት በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ፎረሙ ያሰፈለገበት አላማ ተቋሙ ካለበት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ሰላምን ለማምጣት፣ የማህበራዊ አገልግሎቶችን በቅርበት ለማግኘት፣ችግሮች እንዳይፈጠሩ ለመከላከልና ሲፈጠሩ በዘላቂነት ለመፍታት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን የዋና አስተዳዳሪ አማካሪ እና የዩኒቨረሲቲው የቦርድ አባል የሆኑት አቶ እጅጉ መላኬ እንደተናገሩት ይህ ፎረም የተቋቋመው ለተቋሙ አስፈላጊና በሚፈለግበት ሰአት በመሆኑ ይህንን ሃላፊነት የወሰዳችሁ የተሰጣችሁ ተልዕኮ ከፍ ያለ በመሆኑ የተሰጣችሁን ሀገራዊ ተግባር እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም የፎረሙ አባላት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል እያደረገ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ ለፎረሙ አባላት የተማሪዎች መኝታ ቤት፣የምግብ ቤት፣የመማሪያ ከፍል፣የቤተ መፅሃፍት፣የተማሪዎች ክሊኒክ አገልግሎት የቀድመ ዝግጅት ስራዎችን እንድሁም ዩኒቨርሲቲው በተጓዳኝ እያሰራቸው ያሉትን የግንባታ ስራዎች አስጎብኝተዋል፡፡የፎረሙ አባላትም ዩኒቨርሲቲው ያደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ ይበል የሚያሰኝ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.