የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች ሴቶች ፎረም በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች የልምድ ልውውጥ አካሄደ፡፡

Latest News


ታህሳስ 26/2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች ሴቶች ፎረም ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል ተሞክሮ ለመውስድ በደብረ ማርቆስ፣ኢንጅባራና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች ከታህሳስ10/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የልምድ ልውውጥ አካሂዶ ተመልሷል
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሰራተኞች ሴቶች ፎረም ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰብለወርቅ አበበ እንዳሉትም በተገኘው ተሞክሮ መሰረት የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ከሚመለከታቸው ሃላፊዎች ጋር በመሆን ለማረጋጥ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሸጋው መኮነን እንደገለፁት ዳይሬክቶሬቱ ሴቶች ያሉባቸውን በርካታ ችግሮች ለመቅረፍ በእቅድ ይዞ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ ሴት መምህራንን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን በልምድ ልውውጥ፣በአጭርና በረጅም ጊዜ ስልጠና አቅማቸውን ማጎልበት በመሆኑ የተካሄደው ልምድ ልውውጥ አዳድስ አሰራሮችን ለማወቅና ተነሳሽነትን ለመፍጥር የሚያግዝ በመሆኑ በቅንጅት ስራቸውን አጠናክረው ለመስራት እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
በተገኘው ተሞክሮ መነሻነትም የሴቶች አደረጃቶችን ለማጠናከር እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እንደሚደረግ አቶ ሸጋው ጨምረው ተናግራዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.