የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የከተሞችን ንፅህናን ለመጠበቅ የሚያስችል ግብዓት ማቅረብ ጀመረ

Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በ2012ዓ.ም  የጥናት ትልሞችን  የሙያው ባለቤት በሆኑ የውጭ ገምጋሚዎች አስተችቶ ማፀደቁ የሚታወስ ነው ፡፡ በዚህም መሰረት የጥናትና ምርምር 31፣የማህበረሰብ አገልግሎት 32 እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር 6 በድምሩ ለ69 ፕሮፖዛሎች 5,804,773.7 ብር በጀት ተመድቦ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርገጓል፡፡

በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ከቀረቡትና ከፀደቁት  ፕሮፖዛሎች መካከል አንዱ የዩኒቨርሲቲውን ሁለት ግቢዎች ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ የሚገኙ 11 ወረዳዎችንና 2 የከተማ አስተዳደሮችን ከተሞች የሚበሰብሱና የማይበሰብሱ ደረቅ ቆሻሻዎችን ለይቶ ስርዓት ባለው መንገድ በማሰባሰብ እንደ ቆሻሻዎቹ ባህሪ የማስወገድ፣መልሶ የመጠቀምና ለአፈር ማዳበሪያነት የመጠቀም ስራን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ  ነው ፡፡ በመጀመሪያው ዙር የሙከራ  ስራ ለመስራት ያመች ዘንድ 50 ማጠራቀሚያዎች ተመርተው ወደ አገልግሎት ገብተዋል፡፡ ይህ ፕሮፖዛል ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሲደረግም ከተሞች ለጤና ተስማሚ፣ለኑሮ ምቹና ለእይታ  ፅዱና ማራኪ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጥናታዊ ሀሳቡን አዘጋጅቶ በማፀደቅ ተግባራዊ ስራ የጀመረው መመህር እንድሪስ አህመድ አስረድቷል፡

በተጨማሪም መምህር እንድሪስ እንደገለፀው አሁን የምንገኝበት አለማዊና ሀገራዊ ሁኔታ  እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ እነዚህ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ከቆሻሻ ጋር ያለንን  ንክኪ  በመቀነስ የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል የራሳቸው ድርሻ  ይኖራቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት የከተማ ነዋሪዎች፣አገልግሎት ሰጪና አምራች ድርጅቶች የሚያመርቷቸውን የሚበሰብሱና የማይበሰብሱ ቆሻሻዎች አመቺ ቦታ ላይ ወደተቀመጡት ማጠራቀሚያዎች ለይተው በማስገባት ሀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡የከተሞቹ መዘጋጃ ቤቶችም ማጠራቀሚዎቹ በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን እና ሲሞሉም ቆሻሻው መወገድ ወደሚገባው ቦታ እንዲወሰድ በቋሚነት የሚሰራ አካል መድቦ ማሰራትና ክትትል መድረግ እንዳለበት መምህር እንድሪስ በሰጡት መግለጫ መልዕክታቸውን ጨምረው አስተላልፈዋል፡፡ 

ሚያዚያ 2012ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.