የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ና ማህበረሰብ አገልግሎት የስራ ክፍሉንየትኩረት አቅጣጫዎች አስተዋወቀ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲከፍተኛ አመራሮች፣ዳይሬክተሮች፣የቡድን መሪዎችና መምህራን በተገኙበት የጥናትና ምርምር የትኩረት አቅጣጫዎች   በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው  ከሚሰሩ ስራዎችና ከዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ግብ  የሚነሳ ሆኖየትኩረት አካባቢውንና ነጥቡን በመለየት  የሚሰራ መሆኑን በስራ ክፍሉ ገለፃተደርጓል ፡፡

አቶ አንዷለም በላይ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲየጥናትና ምርምር  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር  ዳይሬክቶሬት የሚሰራባቸውን የትኩረት ነጥቦች  ለይቶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን የትኩረት ነጥቦቹም  የግብርና ምርትና ምርታማነት፣የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ቀጣይነት ያለው የሀይልና ቴክኖሎጅ እድገት፣የማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊና የባህል እድገት ፣የቋንቋና ተግባቦት ጥናት፣ከአካውንቲንግ ቢዝነስና ፋይናንስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣ከስነምግብና ጤና ጋር የተያያዙ ጥናቶች  እንድሁም የሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር  ጉዳዮች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በትውውቁ ወቅት እንደተገለጸው በአሁን ስዓትበጅማሮ ላይ የሚገኙ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ያሉ ሲሆን ለአብነትም የችግኝ ጣቢያ ምስረታ ፕሮጀክት ፣የስነምግብና የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ታሪካዊ ሃብቶችን የመመዝገብ፡የማልማትና የማስተዋወቅ፣ቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ናሽናል ፓርክን የመጠበቅ፣የተቀናጀና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓደ ልማት ፕሮጀክት እንድሁም የተሻሻሉ የደጋ አትክልትና ፋራፍሬ  ዝርያዎችን የማላመድ/በዋናነት አፕል፣የተሻሻሉ የቢራ ገብስና የምግብ ገብስ ፣ስንደ፣ የከብት መኖና ዛፎች/ መሆናቸውም ተገልጸዋል፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ  አቶ ወንድማገኝ አሰፋም ስለማህበረሰብ  አገልገሎት  ምንነት ያለምንም ክፍያ ለማህበረሰቡ የሚሰጥ አገልግሎት መሆኑን ገልጸው  የትኩረት አቅጣጫዎቹም ትምህርት ቤቶችን የማጠናከር፣ስራ ፈጠራን የማበረታታት፣የቆሻሻ ማስወገድ፣የአመራር ክህሎት ማሳደግ፣አርሶአደሮችን የማጠናከር፣የቅርስ አመራር፣የባህልና መቻቻል፣የህገወጥ ስደት እንድሁም የአቅም ግንባታና ግንዛቤ ፈጠራ ተግባራት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡       ጥር 22/2011

Leave a Reply

Your email address will not be published.