የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ተጨማሪ አዳድሰ የምርምር ጣቢያዎችን ተረከበ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው 2011 ዓ.ም የምርምር ስራ ከጀመረባቸው ጣቢዎች በተጨማሪ በ2012 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ከሚያቅፋቸው አካባቢዎች አዳድስ የምርምር ችግኝ ጣቢዎች ውስጥ በቦረና ወረዳ 035 ቀበሌ፣034 ቀበሌና 08 ቀበሌ እንድሁም በለጋምቦ ወረዳ 023 ቀበሌ ሰኞ ገበያ አካባቢ የሚገኙ ቦታወችን  ከየወረዳዎቹ አመራሮች  ከ3ኛ ወገን ነፃ መሆናቸውን አረጋግጦ ተረክቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በነዚህ የምርምር ጣቢያዎች ትኩረት አድርጎ  ከሚሰራባቸው ፕሮጀክቶች ውስጥም የችግኝ ጣቢያ ምስረታ ፕሮጀክት ፣የስነምግብና የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣የተቀናጀና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓደ ልማት ፕሮጀክት እንድሁም የተሻሻሉ የደጋ አትክልትና ፋራፍሬ ዝርያዎችን የማላመድ/በዋናነት አፕል፣የተሻሻሉ የቢራ ገብስና የምግብ ገብስ ፣ስንደ፣ የከብት መኖና ዛፎች/  ለአብነትም  የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

አቶ መሀመድ ጋሹ የለጋምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ  እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የኛው በመሆኑ  ማንኛውንም ማህበረሰቡን ለመለወጥ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በለጋምቦ ወረዳ የ023 ቀበሌ የሰብል ልማት ባለሙያ የሆኑት  ወ/ሮ አለም ፀሀይ ጋሹ  እንደገለጹት የአካባቢው የአየር ንብረት ደጋና በልግ አብቃይ በመሆኑ በእንስሳት ሀብትእና መኖ ልማት  ላይ ዩኒቨርሲቲው ቢሰራ አዋጭ ይሆናል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳሁን አህመድ ቦታዎቹን በተረከቡበት ወቅተ እንደተናገሩት  ዩኒቨርሲቲው በነዚህ እና  ሌሎች በተመረጡ ቦታዎች ላይ የጥናት ምርምር  ስራ በማከናዎን  ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስራ   ይሰራል ብለዋል፡፡

                                      መስከረም 20 �;�e� �

Leave a Reply

Your email address will not be published.