የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የፍኖተ ካርታ እና ስትራቴጅክ እቅድ ትውውቅና ውይይት አካሄደ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲው የ10 አመት ፍኖተ ካርታ እና የ5 አመት ስትራቴጅክ እቅድ ትውውቅና ውይይት የዩኒቨርሲቲው ክፍተኛ አመራሮች፣ዳይሬክተሮች፣ ድኖችና የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት ህዳር 10/2013 ዓ.ም አካሂዷል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ በፕሮግራሙ መግቢያ ባሰሙት ንግግር “ዩኒቨርሲቲው ይህን እቅድ ሊያዘጋጁ ይችላሉ ያላቸውን ዘጠኝ አባላት ያሉት ቡድን አዋቅሮ አጭር ስልጠና እንድወሰዱ ተደርጎ እቅድ መዘጋጀቱን ገልፀው ይህም በየደረጃው በዩኒቨርሲቲው ካውንስል ተገምግሞ፣በቦርድ ደረጃ ከጸደቀ በኋላ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበት ወደ ተግባር የሚገባ ይሆናል“ ሲሉ ገልፀዋል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፍኖተ ካርታ በተቋሙ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ኮሪደር ውስጥ የሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን የሚያመላክት የተቋሙ መሪ ሰነድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ከተለዩት ስትራቴጂያዊ ምሰሶዎች ማለትም የላቀ መማር ማስተማር፣የላቀ ምርምር ፣የላቀ ማህበረሰብ አገልገሎት፣ተቋማዊ እድገት /ልማት/ እና ትብብርና አጋርነት አንፃር ለቀጣይ አሥር ዓመታት በሚታቀዱ የማሻሻያና የስትራቴጂክ አቅጣጫዎች ላይ ኩረት ሰጥቶ ሊሠራባቸው የሚገቡ በርካታ ተግባራት ያሉ መሆኑ ተግልፀዋል፡፡ከቀረበው የእቅድ ትውውቅ በኋላም በቀጣይ የትኩረት ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በርካታ ለ10 አመቱ ፍኖተ ካርታ እና ለ5 አመቱ ስትራቴጅክ እቅድ ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸው መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡በመጨረሻም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኣካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻወል ለተነሱ የግልፀኝነት ጥያቄወችና የመወያያ ሀሳቦች ምላሽ ሰጥተው የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆኗል፡፡ ህዳር 11/ 2013 ዓ/ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.