የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም እና የ2012 ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን አካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀምን ከየስራ ክፍሎቹ አንፃር የተዘጋጀውን አመታዊ የማጠቃለያ ሪፖርት መነሻ በማድረግ የአመቱን  እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ ትኩረት በማድረግ በመስራቱ የጸጥታ ችግር ያለመፈጠሩ፣በዩኒቭርሲቲው ለታቀፉ  ወረዳዎች የተጠናከረ የማህበረሰብ አገልግሎት መኖሩ፣በተመረጡ ወረዳዎች መምራህን የምርምር ስራ መጀመራቸው፣ተጨማሪ የዶርሚታሪ ግንባታ መካሄዱ የሚሉት በጥንካሬ የተጠቀሱ ናቸው፡፡መሻሻል ካለባቸው መካከል የተግባር ትምህርት ለመውጣትና ለምርምር ስራ  ያጋጥሙ የነበሩ የትራንስፖርት ችግሮች ያለመቀረፍ፣በግዥ መጓተት የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር መኖር እንድሁም ተቀናጂቶና ተናቦ

ተግባራትን ያለመፈጸም የሚሉት በቀጣይ መስተካከል አለባቸው ተብለው ከተጠቀሱት መካከል የገኙበታል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ አቶ አሊ እንድሬ እደተናገሩት የተግባራት መቆራረጥ መነሻው ሀላፊነትን በአግባቡ ያለመወጣትና ሀገራዊ ያለመረጋገትን እንደምክኒያት በመውሰድ የባለቤትነት ስሜት ባለመንፀባረቁ  በመሆኑ በቀጣይ  ሁላችንም ችግሮቻችንን ቀርፈን  ለጋራ ውጤት መትጋት ይገባል  ብለዋል፡፡  

 የዩኒቨርሲተው ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ታምሬ ዘውደ   በገለጹት የማጠቃለያ  ንግግር የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀማችንን መገምገም ለ2012 ስራ መሳከት ትምህርት የምንወስድበትና ለበለጠ ስኬት የምንነሳሳበት ይሆናል ብለዋል፡፡ 

                                    መስከረም 17/201 ht:9����

Leave a Reply

Your email address will not be published.