የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቅ አመት እቅድ አፈፃፀምን ከየስራ ክፍሎቹ አንፃር የተዘጋጀውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የ6 ወሩን እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡በተማሪዎች መካከል ተፈጠሮ የነበረው መጠነኛ ብጥብጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩን ያወከ መሆኑ፤ የሳይንስ ቤተ ሙከራ ክፍል ቁሳቁሶች በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተገዝተው የቀረቡ ቢሆንም በወቅቱ አለመገጠማቸው፣ በግዢ ስርዓቱ ምክንያት የሚያስፈልጉን ቋሚ እና አላቂ ንብረቶች ማሟላት አለመቻሉ፣ለተግባር ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች እጥረት መኖር፣የመብራት መቆራረጥና የውሃ እጥረት (መካነ ሰላም) በሁለቱም ካምፓሶች አጥር የሌለ መሆኑ ና ግንባታ አለመጀመሩ የዩኒቨርስቲውንሰላም ለማስጠበቅ እንቅፋት መሆን የሚሉት በዋናነት ያጋጠሙ ችግሮች ተብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡
ዶክተር ሺበሺ አለባቸው የመካነሰላም ካምፓስ ዳይሬክተር በስብሰባው ወቅት እንደገለጹት ምንም እንኳን ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ መማር ማስተማር እንዳይኖር በርካታ እንቅፋቶች ያጋጠሙት ቢሆንም በተደረገው የጋራ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የተሻለ አፈፃፀምም መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲተው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘውደ በገለጹት የማጠቃለያ ንግግርም በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈን የሚፈለገውን ስኬት መፈፀማችን የሚያስመሰግን ሲሆን ለቀጣይም ከሰላም አንፃር ችግሮች እንዳይገጥሙ እኩል ድርሻ በመውሰድ ተማሪወቻችንን ማስመረቅና ሴሚስተሩን በጥሩ ስኬት ማጠናቀቅ መቻል አለብን ሲሉ መልዕካታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 
የካቲት 8/2012

Leave a Reply

Your email address will not be published.