የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀመረ፡፡

Latest News


የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ STEM (Science, Technolog, Engenering, and Mathmatics center)ማዕከል በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በዚያው አመት የቴክኖሎጅ ሳምንት በማዘጋጀት ከትምህርት ቤቶችና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተወጣጡ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች እንድወዳደሩና እንድበረታቱ አድርጓል፡፡ማዕከሉ በጦርነት ውድመት ከደረሰበት በኋላ በአሁን ሰዓት stem power የተባለ ሀገር በቀል ድርጀት ባደረገለት ድጋፍና ዩኒቨርሲቲው በሰጠው ትኩረት የላብራቶሪ እቃዎችና አስፈላጊ ግብአቶች ተሟልቶለት ወደ ስራ እንድገባ ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት በ2014ዓ.ም በክረምት መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ በዙሪያው ከሚገኙ 38 የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 110 ተማሪዎች የባዮሎጅ፣የኬሚስትሪ፣የፊዚከስ፣የሂሳብና የኤሌክትሮኒከስ ትምህርቶችን በተግባር በተደገፈ መልኩ እያስተማረ ይገኛል፡፡የዩኒቨርሲቲው ኢንዱስትሪ ግንኙነትና የቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አበጋዝ ትዛዙ (ዶ/ር) እንደተናገሩትትምህርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በክረምት መርሐ ግብር ከሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲውም የተማሪዎችን የምግብ፣ የመኝታ እና የመማሪያ ቁሳቁሶችን ወጭ ሽፍኖ እያስተማረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የተሻለ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች መክረምት መርሃ ግብር እንድማሩ ያስፈለገበት ዋና ጉዳይ የሳይንስ እውቀታቸው እንድያድግ፣ከቴክኖሎጅ ጋር እንድተዋወቁና የፈጠራ ክህሎታቸው እንድዳብር ለማድረግ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የትምህርት አሰጣጡን ለየት የሚያደርገውም ተማሪዎች እስካሁን ከመጡበት በተለየ መልኩ ሳይንሱን በተግባር ማየትና መለማመድ የሚያስችላቸው መሆኑን አበጋዝ (ዶ/ር) አክለው ተናግረዋል፡፡ትምህርቱን ሲከታተሉ ያገኘናቸው ተማሪዎች እንደተናገሩትም የትምህርት አሰጣጡ ከንድፈ ሃሳብ ይልቅ ተግባራዊ ልምምድ ላይ ትኩረት የሚያድርግ በመሆኑ አዳድስ እውቀቶችን እንዳገኙና ከቴክኖሎጅ ጋር እንድተዋወቁ አስችሏቸዋል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.