የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ በሁለቱም ካምፓስ የሚገኙ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎቹን በተለያየ የትምህርት መስኮች በመደበኛ ያሰለጠናቸውን 1267 ተማሪዎችን ነሀሴ 22/2013 ዓ.ም በዋናው ካምፓስ ቱሉአውሊያ እና ነሀሴ 23/2013 ዓ.ም በመካነሰላም ካምፓስ የክብር እንግዳው የፌድራል ኮንትራክሽን ሚኒስቴር ሚስትር ድኤታ ዶክተር መስፍን አሰፋ ተመራቂ ተማሪዎችና የተመራቂ ተማሪዎቸ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነስላም ግቢ ጀነራል ዳይሬክተር ዶ/ር ሽበሽ አለባቸው ባደረጉት ንግግር ሀገራችን አሁን የገጠማት ችግር ዋና ምክንያት የኢትዮጵያ ጥላቶች በዘረኝነት ለረጅም ጊዜ የመከፋፈል ሴራ ውጤት በመሆኑ በጋራ አንድ ሆነን ሀገራችንን ከጥፋት ልንታደግ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የመቅደላ አምባዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘውደ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከጅማሮ ጀምሮ እስካሁን የነበሩበትን ተግዳሮቶችና አሁን የደረሰበትን ስኬት አንስተው የዛሬ ተመራቂዎች ለዚህ ልዩ ቀን መድረሳችሁ የስኬት መጨረሻ ሳይሆን ጅማሮ በመሆኑ በቀጣይ እራሳችሁን በማሻሻል ለሀገራችሁ የድርሻችሁን እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

                                                                   ነሃሴ 22/2013 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.