ነሃሴ 22 /2014 ዓ.ም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዙር ተማሪዎቹን በመደበኛው መርሀ ግብር በሁለት የትምህርት መስኮች (ኮምፒዩተር ሳይንስና ጅኦሎጂ) 73 ተማሪዎችን እንድሁም በተከታታይ (ቅዳሜና እሁድ) መርሀ ግብር 21 ተማሪዎችን እና በ HDP ፕሮግራም 31 የዩኒቨርሲቲው መምህራንን ነሀሴ 21/2014 ዓ.ም በዋናው ካምፓስ ቱሉ አውሊያ እንድሁም ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በመካነሰላም ካምፓስ በተከታታይ (ቅዳሜና እሁድ) መርሀ ግብር 159 ተማሪዎችን የክብር እንግዶች ፣የተመራቂ ወላጆች፣የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ፣ተመራቂ ተማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳና የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ም/የቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ከፍያለው አለማየሁ ባደረጉት ንግግር የዛሬዋ ምረቃ ላይ ለመድረስ ብዙ ውጣ ወረድ እንዳለፋችሁ ሁሉ ዘመኑ የውድድር በመሆኑ ብዙ በማንበብ ፣በመመራመርና ስራ ሳትንቁ በመስራት ከራሳችሁ አልፎ ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ እንድሆኑ አሳስባለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ በበኩላቸው እንደተናገሩት ተማሪዎች በጦረነት፣በኮሮና በሌሎች ችግሮች ውስጥ አልፈው ለዚህ ቀን መብቃታቸው ትልቅ ኩራት መሆኑን ገልጸው ለህይወታችሁ ሌላ ምዕራፍ መክፈቻ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ ለዚህም ቀን መድረስና መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በእለቱ ተማሪ ፋንታሁን አድማስ ከጅኦሎጅ ትምህርት ክፍል 3.98 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ከሴቶች ደግሞ ተማሪ መሰረት ምህረት 3.9 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!










