የመቅዳለ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የአካዳሚክ የደረጃ እድገት ሰጠ፡፡

Latest News

ነሃሴ /2014 የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ቱሉ አውሊያ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በቀን 29/10/2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የትምህርት ሚኒስቴር ጥቅምት 4/2014 ባጣው መመሪያ (harmonized standard for academic staff in public university) መሰረት ከትምህርት ክፍል ጀምሮ የቀረበው መረጃ በኮሌጅ መማክርትና በሴኔት ስታንዲግ ኮሚቴ ከታየ በኋላ ዶ/ር ካሳ ሻውል መስፈርቱን የሚያሟሉ በመሆኑ በ”Animal nutrition” ትምህርት ዘርፍ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል፡፡ሴኔቱ ለዕድገቱ የሚያበቁ መሰፈርቶችን ማለትም የማስተማር ብቃት፣ የህትመት ውጤት፣ የፈጠራ ስራ ፣ሙያዊ የማህበረሰብ አገልግሎት፣በዩኒቨርሲቲ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግና ሌሎች መመዘኛዎችን መሰረት በማድግ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማረጉን ሰጥቷል፡፡ ዶ/ር ካሳ ሻውል ረታ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ የመጀመሪያ ከፍተኛ የአካዳሚክ ደረጃ እድገት የተሰጣቸው መሆኑ እንዳስደሰታቸው ያነጋገርናቸው የሴኔት አባላት ገልጸው የተገኘው እድገት ለግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ለዩኒቨርሲቲውም ከፍታ ወሳኝ በመሆኑ ሌሎቹም የእርሳቸውን ፈለግ በመከተል ስራቸውን በቅንነትና ታማኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አክለው ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.