የመቅዳላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ስላማዊ የመማር ማስተማር ስራውን ጀመረ

Latest News

በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማኮላሸት ና አቅጣጫውን ለመቀየር ቀና አመለካከት የሌላቸው ሀይሎች በሚሰጡት ተልዕኮ በማንነታችን በመግባት እየከፋፈሉ ግጭቶችን በማስነሳት ሀገራችን እንዳትረጋጋ በማድረግ ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነው ፡፡ በመሆኑም የሀገራችንን ወጣቶችና የነገዋን ኢትዮጵያችንን ተስፋዎች ከአላማቸው በማውጣት መጠቀሚያቸውም  እያደረጓቸው ይገኛሉ ፡፡

ይህንኑ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎችና ዩኒቨርሲቲዎች የፈጠሩትን ምክኒያት አልባ ግጭቶችና ሁከቶች መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲያችንም ከህዳር  5/03 /2012 ዓም  ጀምሮ ያደረጉት የብጥብጥና ሁከት  ሙከራ በቅን አሳቢ ተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞቻችን ፣የጥበቃ ሃይሎቻችን ፣በአመራሮቻችንና የከተማ ነዋሪዎቻችን  ጥምረት  ምንም አይነት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሳይፈጠር ለማረጋጋት በመቻሉ ዩኒቨርሲቲው በዚሁ  አጋጣሚ ምስጋናውን ያቀረባል ፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት በሁለቱም ግቢዎቻችን ሰላማችን ወደ ቀዶሞው ሁኔታ ስለተመለሰ ከሰኞ 9/03/2012 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር  ስራው ጀምሯል፡፡ በዚሁ መሰረት ከህዳር 10/03/2012 ዓም ጀምሮ ሁሉም ተማሪዎች በመደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችሁ መሰረት  በመማሪያ ክፍላችሁ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ ዩኒቨርሲቲው በታላቅ አክብሮት ጥሪውን  ያስተላልፋል ፡፡

                                                               ህዳር 10/2012

Leave a Reply

Your email address will not be published.