የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነፃነት/ኦቶኖሚ ማዕቀፍ/ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

Latest News

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የመንግስትከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻነት /ኦቶኖሚ ማዕቀፍ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ማለትም ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡በሰነዱ ላይ ገለጻያደረጉትየመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻዎል እንደተናገሩትየዚህ ማዕቀፍ ዋና ዓላማው የመንግስት የከፍተኛትምህርትተቋማትን ተልዕኮ እና ራዕይ ለማሳካት ተቋማዊ ነፃነት ስርዓትን እና ተጠያቂነትን በማስፈን የትምህርት ጥራትን፣ አግባብነት፤ፍትሃዊነት፣ ውጤታማነት፣ ተወዳዳሪነትና ቅልጥፍናን በማሳደግ ተቋማትን ትራንስፎርም ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነትን ከተጠያቂነት ጋር በመስጠት ውጤትን መሰረት ያደረገ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የተሰጣቸውን ተልዕኮ እንዲወጡ በማገዝ የትምህርት ተደራሽነትና ፍትሐዊነት፤ የትምህርት ጥራትና ተገቢነት፤ ጥናትና ምርምር፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሰሩ ማድረግ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት ተገልፀዋል፡፡

1 thought on “የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነፃነት/ኦቶኖሚ ማዕቀፍ/ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.