የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ለተመራቂ ተማሪዎች ግንዛቤ ተፈጠረ ፡፡

Latest News

ህዳር 8/ 2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም የሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተመረቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ተመርቀው ከመውጣታቸው በፊት የመውጫ ፈተና እንደሚሰጡ መመሪያ አውርዷል፡፡በዚሁ መሰረት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በግብርና እና በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጆች ስር ለሚገኙ የትምህርት ክፍል የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን አስመልከቶ ግንዛቤ ፈጥሯል ፡፡የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነጋ ከሰተ በውይይቱ ወቅት የ2015ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የሚዘጋጁበትን ዝርዝር የትምህርት ይዘቶች፣ የተፈቀደውን የዝግጅት ጊዜና የመውጫ ፈተና ዝግጅትን በተመለከተ ለተማሪዎች ግንዝቤ ፈጥረዋል ፡፡የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ስማማው ምኒይልህ በኮሌጁ ስር ለሚገኙ ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች ከወዲሁ ቀድመው የሚዘጋጁበትን ሞጁል ከማዘጋጅት እስከ ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ድረስ አስፈላጊውን ዕገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል ፡፡የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት አያያዝ ኮሌጅ ዲን አቶ ደጉ አባት በበኩላቸው ለፈተናው ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በኮሌጁ ስር ያሉ ሁሉም ትምህርት ክፍሎች ተመራቂ ተማሪዎችን ለምርቃት ከማብቃት ጎን ለጎን ለመውጫ ፈተናውም ማገዝ እንደሚገባ እና ተማሪዎች ቀሪ ጊዜያቸውን በአግበቡ በመጠቀም ለመውጫ ፈተናው ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ፡፡ተማሪዎች በበኩላችው በዩኒቨርሲቲው በኩል መሟላት ያለባቸው የሞጁል ዝግጅት ፣ የዲጅታል ቤተ መጽሀፍ አገልግሎት ፣ ኮረሶችን መሸፈን፣ በቤተ ሙከራ የሚሰሩ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.