የምርጥ ዘር እጥረትን ለመቅረፍ በክላስተር ለተደራጁ አርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News Research news


መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሲሪንቃ ግብርና ምርምር ማእከል እና ከደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ጋር በመተባበር በጃማ፣ ወግዲ እና ቦረና ወረዳዎች የጤፍ እና ቦሎቄ ሰብሎች የማስፋት ስራ ለመስራት በክላስተር ለተደራጁ አርሶ አደሮች ሰኔ 25/2013 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበበ ምስጋናው እንደተናገሩት ‹‹የዚሀ ስልጠና ዋና አላማ በአማራ ክልል ብሎም በወሎ አካባቢ የሚታየውን የምርጥ ዘር እጥረት ለመቀረፍ በ115 ሄክታር መሬት ላይ በክላስተር ለተደራጁ አርሶ አደሮች ሙከራ በማድረግ የማስፋት ስራ ለመስራት ››እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሲሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ጌታቸው በበኩላቸው በዚህ የምርጥ ዘር የማስፋት ስራ ላይ ወግዲ ወረዳ ዞብል ጤፍ በወይና ደጋ አካባቢ፤ጃማ ወረዳ ህብር 1 የደጋ ጤፍ እና በቦረና ወረዳ አዋሽ 2 ቦሎቄ ቆላማ ቦታዎች በክላስተር የተደራጁ አርሶ አደሮች ዘንድ ሙከራ እንደሚደረግ ገልፀው፡ ዘሩን በአጭር ቀን ውስጥ በአርሶ አደሮቹ እጅ ለማሰገባት ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.