የምሰራቅ አማራ ዩኒቨርሲቲዎችና በቀጠናው የሚገኙ የምርምር ማዕከላት በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ ፡፡

Latest News Research news

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ምስራቅ አማራ የሚገኙ ፡- የወልድያ ፣ ወሎ ፣መቅዳላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ፤የሲሪቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ፤የደሴ የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብአቶች ቁጥጥር ኳራንታይን ማዕከል :የሰሜን ወሎ ፣ደቡብ ወሎ ና ኦሮሚያ ልዩ ዞኖችን ያካተተ ‹‹ ህብረት ለዘላቂ ልማት ›› በሚል መሪ ቃል በቅንጅት ለመስራትየሚያስችል የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ፡፡የስምምነት ሰነዱ፡ በህብረት በመስራት መሬት የነካ ጥናትና ምርምር ና ማህበረሰብ አገልግሎቶችን በማጠናከር በቀጣ በጋራ አብሮ ለመስራት የሚያስችል እቅድ በማቀድ ወደ ተግባር ማስገባት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጾዋል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨረሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ በውይይቱ የመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደገለጹት ‹‹ በቀጠናው የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ና የምርምር ማዕከላት የምንገኝበት ቀጠና የሰብል ፣የእንስሳት እና የአትክልትና ፍራፍሬ ከባቢ በመሆኑ የማህበረሰቡን ምርታማነት የሚያሳድጉ ና አካባቢውን የሚቀይሩ ጉዳዮች ላይ ስነምምነት በመድረስ ልንሰራ ይገባል ›› ሲሉ ተናግርዋል ፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲየጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን አህመድ በበኩላቸው ዩኒቨርሰቲው በአቀፋቸው ወረዳዎች እየተሰራ ያለውን የምርምር ና ማህበረሰብ አገልገሎት ስራዎችን በማቅረብ ዩኒቨረሲቲው እየሄደበት ያለውን ርቀት ለውይይት ተሳታፊዎቹ አሰገንዝበዋል ፡፡ለወይይት መነሻ የሚሆን የጋራ ፎረሙ እቅድ ቀረቦ የእለቱ የውይየት ተሳተፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ስምምነት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል

Leave a Reply

Your email address will not be published.