የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ልዑክ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የቅድመ ዝግጀት ስራውን ድጋፍና ክትትል አደረገ ፡፡

Latest News

ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስተማማኝ የሆነ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት ወይም ህክምና እስከሚገኝ ድረስ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ተዘግተው የነበሩ የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን በመክፈት የተቋረጠውን የትምህርትና ስልጠና እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል የቅድመ ዝግጀት ስራ እንድስራ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰጠው ተልዕኮ መሰረት መቅደላ አምባ ዩኒቨረሲቲ በመገኘት የቅድመ ዝግጀት ስራውን ድጋፍና ክትትልአድርጓል ፡፡በክትትሉም ወቅት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል ባደረገው ቅድመ ዝግጀት ከኮሮና ቫይረስ ንኪኪ ነጻ በሆነ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጠናል ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን አብርሃ አስተያተቸውን ሰጥተዋል ፡፡ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ጋር በተያያዘ የተማሪዎች መኝታ ቤት አንድ ዶርም 2 ተማሪ ፣በቤተ መጽሀፍት አንድ ወንበርና 1 ጠረጴዛ ለ1 ተማሪ ፣በመማሪያ ክ ፍል ወስጥ አንድ ወንበር ለአንድ ተማሪ ሆኖ በመምህሩና ተማሪው መካከል ያለው እርቀት ቀይ መስመር የተዘጋጀ ከመሆኑም በላይ በዩኒቨርሲቲው መግቢያ በር የእጅ መታጠቢያ የተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል ፡፡ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት ካውንስል ጋር የጋራ ውይይት በማድረግ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የተፈጠረሲሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት አድረጎ ሊያግዝበት ከሚገባው ጉዳይ መካከል ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ፤ለዩኒቨርሲቲው የተሸከርክሪ እጥረትን መቅረፍ ፤ያልተስተካከሉ የስራ መደቦችን ከማስተከከል አኳያ ትኩረት ሰጥቶ እንዳግዝ የማኔጅመንት የካውንስሉ አባላት አሳስበዋል ፡፡በማጠቃለያውም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታመሬ ዘውደ እንዳሳስቡትየምናስተካክላችውን ተግባራት ቀድመን በትኩረት በመስራትና ያሉብንን ችግሮች እያሳሰብን ተማሪዎችን ለመቀበል ሁሉም አካልየበኩሉን ጥረት ማድረግ አለበት ያሉ ሲሆን በዋናነትም በገቢው ውስጥ ለስራ የሚገባ አካል የፊት መሸፈኛ ማክስ ፣ሳኒታይዘር እንድሁም በመግቢያ በሩ ላይ በተዘጋጅው የእጅ መታጠቢያ እጁን በውሃና ሳሙና በመታጠብ ኮሮናን በመከላከል ተልኳችንን እንድንውጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.