የስራ አመራር ስልጠና ተሰጠ

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር በአካዳሚኩ ዘርፍ ለሚሰሩ ዳይሬክተሮች፣ኮሌጅ ዲኖች፣የትምህርት ክፍል ሃላፊዎች እና አስተባባሪዎች ከየካቲት 12-14/2013 ባሉት ተከታታይ ቀናት ሰልጠና ተሰጥቷል፡፡የስልጠናው ዋና አላማ በአካዳሚክ ዘርፍ ለሚሰሩ ልዩ ልዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች በሚሰሩት ላይ የአመራር ብቃትን ለማሳደግ፤በራስ መተማመንን ለማሳደግ እና የራስ የህይወት ተሞክሮን ከስራው ጋር አዋህዶ አያይዞ ሊሰራ የሚችል የአምራር አቅም ለመገንባት እንደሆነ ተገልጾዋል ፡፡የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ካሳ ሻወል በመክፍቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ስልጠናው ‹‹ካለን ዕውቅትና ክህሎት በተጨማሪ በስራ ክፍላችን የምንምራውን ሰው በተሻለ ዕውቅትና ክህሎት በመምራት የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እና ተልዕኮዎቻችንን በተገቢው መንገድ ለመፈፀም የአቅም ግንባታ ሰልጠናዎችን እንዳስፈላጊነቱ መስጠት ወሳኝ ሆኖ ስለተገኘ ነው ›› ሲሉ ተናግረው በቀጣይም የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን አመችችቶ በመስጠት የአመራሩን አቅም ማሰደግ ችላ የማይባል ስራ እንደሆ አክለው ተናግረዋል። የካቲት 16/2013 ዓ.ም ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት፡-website- https://mkau.edu.et/fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.Universitytwitter- https://twitter.com/mekdela_ambaLinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mauYouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!3,989People Reached357EngagementsBoost Post

79794 Comments8 SharesLikeCommentShare

Leave a Reply

Your email address will not be published.