የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት የ2014 ዓ’ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015ዓም እቅድ ኦረንቴሽን አካሄደ።

Latest News

በግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነሰላም ካምፓስ ጀነራል ዳይሬክተር ሺበሽ አለባቸው( ዶ/ር ) የፀረሙስና ትግል ፍሬያማ የሚሆነው አዕምሮ ሲለወጥ በሆኑ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ፈንታው የዳይሬክቶሬቱን የ2014 ዓ’ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015ዓም እቅድ ኦረንቴሽን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት የፕሮግራሙ ዋና አላማ በፀረሙስና ትግሉ ያከናወኗቸውን መልካም ጅማሮዎች ለማስቀጠልና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ተልዕኮ በመውሰድ ወደ ስራ ለመግባት መሆኑን ገልፀዋል።በቀጣይም የምክክር መድረኮችን በመፍጠር ግንዛቤ መፍጠር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡትን ተጠያቂ ማድረግ፣በየደረጃው የግንዛቤ ፈጠራ ተግባራትን በማከናወን ሙስናን መከላከል፣አርአያ የሆኑ ግለሰቦችን እውቅና መስጠት፣ደንበኞች ጥቆማ እንድሰጡ ማበረታታት፣ልዩ ልዩ የፀረሙስና አደረጃጀቶችን መፍጠር፣ የፀረሙስና ቀንን በማክበር ለግንዛቤ ማሳደጊያ መጠቀም እና ለአድስ ገቢ ተማሪዎች የስነምግባር ሰልጠና መሰጠት የሚሉት በ2015 ዓም በትኩረት መሰራት የሚገባቸው መሆናቸውን አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.