የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ አመት የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማላይያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት እና የተወሰዱ መፍትሄዎችን በማስቀመጥ የስድስት ወሩን የስራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡የዩኒቨርሲቲው የእቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሃይሌ የስጋት የ6 ወሩን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የተፈቀዱ የስራ መደቦች በቂ የሰው ሃይል አለመገኘት፤በግዢ ስርዓቱ ምክንያት የሚያስፈልጉን ቋሚ እና አላቂ ንብረቶች ማሟላት አለመቻሉ፤ዓለም አቀፍ ክስተት ኮቪድ 19 ምክንያት በተቀመጠዉ ካሌንደር መሠረት የመማር ማስተማር ችግር መፈጠር፤የመብራትና የኢንተርኔት መቆራረጥ፤በአንዳንድ የስራ ክፍሎች ተናቦ አለመስራት፤የሰው ሀይል መልቀቅ፤በአንዳንድ ሠራተኞች ላይ የሥራ ተነሣሽነትና የአገልጋይነት መንፈስ ማነስ እንድሁም በየደረጃው በቂ የሆነ ክትትልና ድጋፍ አለማድረግና ግብረ መልስም ያለመስጠት ውስንነት መኖር የሚሉት በዋናነት ያጋጠሙ ችግሮች ተብለው የተነሱ ናቸው፡፡የሰው ሃይል እጥረት ባለባቸው ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውን መቅጠር፤የኢንተርኔ አገልግሎት በተቻለ ፍጥነት እንድኖረን የተለያዩ አካላትን ግፊት ማድረግ እና የግዥ ስርዓቱ የተሳለጠ እንድሆን ጥረት ማድረግ የሚሉት የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ተብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡በቀረበው ሪፖርት ላይ ከታዳሚው ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች የማጠቃለያ ምላሽ ተስቶበት ግምገማው ተጠናቋል፡፡ የካቲት 24/2013 ዓ.ም

website- https://mkau.edu.et/fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.Universitytwitter- https://twitter.com/mekdela_ambaLinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mauYouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.