የባህል ማዕከል ግንባታ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

Latest News

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረስብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በዙሪያው ከሚገኙ ወረዳዎች ባህል፣ ቅርስና ሀገር በቀል አውቀቶችን ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችል ማዕከል ለመገንባት በመካነ ሰላም ግቢ የመሰረት ድንጋይ አሰቀምጧል ፡፡ግንባታውን ለመጀመር በዩኒቨርሲቲው ቴማቲክ ኤሪያ የሚገኙ 11 ወረዳዎች የራሳቸውን ባህል የሚውክሉ ቤቶችን ለመገንባት የደቡብ ወሎ ዞን ባህልናቱሪዚም መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን መኮነን በተገኙበት የየወረዳው የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊዎች እጣቸውን በማንሳት የቤት መገንቢያ ቦታቸውን ተረክበዋል ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ማህበረስብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን አህመድ እንዳሳሰቡት ለወረዳዎች የቤት መገንቢያ ቦታ በእጣ ያስረከብንበት ዋና አላማ ፡- ዩኒቨርሲቲው ግንባታውን ለመጀመር የየወረዳውን ባህል የሚወክል የቤት ግንባታ ትክክለኛውን ሞደል ከወረዳው የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶችና የሚመለከታችውን የስራ ኃላፊዎች አስተያየት በመቀበል ወረዳውን የሚወክል መሆኑን ይበልጥ አረጋግጠን ግንባታውን ለመጀመር ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.