“ለአለም ያለንን አበርክቶ እያሰብን አካባቢያዊ የፈጠራ ስራን ለማበረታታት በጋራ እንሰራለን!” በሚል መሪ ቃል የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ወሎ ምዕራባዊ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን እና መምህራንን የፈጠራ ስራቸውን እንድያቀርቡ በመጋበዝ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሳምንትን ለመጀመሪያ ጊዜ አክብሯል፡፡በዕለቱም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማዕከል/Science,Technology,Engineering,Mathematics/ STEM Center/ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳሁን አህመድ የቴክኖለጂ ፈጠራ ሳምንትና የማዕከሉ መከፈትን አስመልክቶ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር “ከሁሉም ወረዳዎችና ከዩኒቨርሲቲያችን የፈጠራ ስራ ያላቸው ተማሪዎችና መምህራንን ለማበረታታት፣ አንዱ ከሌላው እንድማማሩበት ቀጣይነት ባለው መልኩ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በዚህ ማእከል በማሰባሰብ ለላቀ ውጤት እንድበቃ ለማድረግ ይህ የቴክኖሎጅ ሳምንት እንደ አይን መክፈቻ ሆኖ ተዘጋጅቷል” ያሉ ሲሆን አክለውም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአንድ ማዕከል በማደራጀት ለማገዝ፣ለማበረታታትና ለመሸለም ከጎናችሁ ነን በማለት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ላቀረቡ ወጣቶች ቃል ገብተዋል፡፡
በዚህ ሲምፖዚየም ቦረና ፣ ወግዲ፣ ለጋምቦ፣ተንታ፣ መቅደላና ወረኢሉ ወረዳዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ያቀረቡ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የቴክኒክ ኮሚቴ ስራዎቹን አወዳድሮ ባቀረበው ውጤት መሰረት ተማሪ ነኢማ እንድሪስ ከወረኢሉ ወረዳ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች ፡፡
የካቲት 15/2013 ዓ.ም
ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA
ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!