የቴክኖሎጅ ፈጠራ ክበብ በመካነ ሰላም ግቢ ተቋቋመ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅና ፈጠራ ባልተቤቶችን በመለየት የፈጠራ ችሎታቸውን ወደ ተግባር እንድቀይሩ ለማድረግ የገቢዎን ተማሪዎች በክበብ አደራጅቷል ፡፡ የክበቡ ዋና አላማ የግቢውን ተማሪዎች በክበብ በማደራጀት ቴክኖሎጅና ፈጠራ ስራዎችን በተግባር እንዲያሳዩ ለማድረግ ነው ፡፡የመካነ ሰላም ግቢ ጀኔራል ዳይሬክተር ዶ/ር ሽበሽ አለባቸው ክበቡ በተቋቋመበት ወቅት ተገኝተው እንደተናገሩት‹‹ የዕለት ከዕለት ክንውናችን በቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት ውጤቶች ላይ ያተኮረ መሆን አለበት›› ሲሉ ተናግረው ተማሪዎች በዚህ አይነት ተግባራት ተሳታፊ በመሆን ዘመኑ ካፈራው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውጤቶች ላይ የራሳችሁን ፈጠራና ክህሎት በመጨመር የዕለት ከዕለት ክንውናችሁን ቀላል የሚያደርግ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ሽግግርና ኢንዱስተሪ ግንኙነት ዳይሬክተር መ/ር ዳዊት ድበኩሉ በበኩላቸው የክበቡ መቋቋም ተማሪዎች ያላቸውን እምቅ ችሎታ ወደተግባር በመቀየር እድል እንደሚፈጥር አክለው ገልጸዋል ፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.