የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ክፍሎች እውቅና ሰጠ፡፡

Latest News

በቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሁሉቱም ግቢዎች የሚገኙ አመራሮች፣መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በአንድ አመት ተክፍሎ የሚያልቅ የአንድ ወር ደመወዛቸውን በየወሩ ተቆራጭ በማድረግ ለህግ ማስከበርና ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ እያደረጉ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላደረገው ድጋፍም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት “በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻ የተከፈለ መሰዕዋትነት ለኢትዮጵያ ሉአላዊነትና አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ባዘጋጀው የእውቅና ፕሮግራም ላይ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡እስከ ሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም ድረስም 50 ኩንታል ዱቄት፣50 ኩንታል ሩዝ፣600 ደርዘን ውሃ እና 745 ሊትር ዘይትና 20 ሰንጋ በሬዎች በድምሩ በገንዘብ 553,500.85 /አመስት መቶ አምሳ ሶስት ሺ አምስት መቶ ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም/ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከወጭ ቀሪም 3,586,517.42/ ሶስት ሚሊየን አመስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺ ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም / እንድሁም የግንቦትና የሰኔ ወራትን ምዋጮ ጨምሮ በቀጣይ ለድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን የድጋፍ አስተባበሪ ኮሚቴው ገልዋ፡፡ ግንቦት 2014 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.