የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

Latest News Research news

ታህሳስ /2015 የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራው መነሻም ከዩኒቨርሲቲዎች ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት በመሆኑ ድሆችን በመለየት ቤታቸው እንድታደስ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት፤በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች አነሳሽነት ስራው መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሰረት አበበ አስታውቀዋል፡፡ቤቶችን የማድስ ስራው በጊምባና በመካነሰላም ከተማ አስተዳደሮች የሚካሄድ ሲሆን ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመሆን የጋራ ውይይት ተካሂዶ በከፋ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግር ውስጥ የሚገኙ በጊምባ ከተማ አስተዳደር 10 ቤቶች ፣ በመካነሰላም ከተማ አስተዳደር 4 ቤቶች የተለዩ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅም በድምሩ 14 በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካሞችንና ቤተሰቦቻቸውን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.