የኢንዱስትሪ ትስስርን በማጠናከር የተግባር ትምህርት እየተሰጠ ነው፡፡

Latest News

መቅዳላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመባቸው ተልዕኮች አንዱ የሆነው ጥራትያለውና በተግባር የተፈተሸ ትምህርት በመስጠት በእውቀት ፣በክህሎትና በአመለካከት ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ምሩቃንን ማፍራት ነው፡፡ይህንን ተግባር እውን ለማድረግ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር እንድያጎለብቱ የማድረግ ስራ እየሰራ ይገኛል ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአቅራቢያው ከሚገኙ በሀገር አቀፍና በአለም ደረጃ እውቅና ካላቸው የመንግስትና የግል ፋብሪካዎች ጋር ግንኙነቱን በማስተሳስር ተመራቂ ተማሪዎች የተግባር ተምህርት እንዳገኙ ለማድረግ ጠንክሮ እየሰራ ነው፡፡
በግብርና ኮሌጅ ስር የሚገኘው የግብርና ምጣኔ ሃብት ትም/ ክፍልም የ4ኛ አመት ተመራቂ ተማሪዎችን በሀገር ደረጃ እውቅና ካላቸው የመንግስትና የግል ፋብሪካዎች በኮምቦልቻ ብረታብረት ፋብሪካ፣በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪያል ፓርክ፣ በኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና በቢንማስ የእንስሳት መኖ ሜሽ ፤በክሪምብል እና በፔሌት ማምረቻ ፋብሪካ በአካል ተገኝተው የጥሬ እቃና ምርት አመራረት የተግባር ትምህርት እንዳገኙ ተደርጓል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የግብርና ምጣኔ ሃብት ት/ት ክፍል ሃላፊ መምህር በላይነህ ዮሃንስ እንደተናገሩትም የትምህርታዊ ጉዞው ዋና አላማ ተማሪዎችን በንድፈ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር የተደገፈ እውቀት ለማስጨበጥ/to equip students with practical knowledge/ የሚመለከታቸውንና ከትምህርት ክፍሉ ጋር ትስስር ያላቸውን ድርጅቶች በመለየት አሰራራቸውን፣የሃብት አጠቃቀማቸውን፣ የገበያ ሁኔታውን፣ለማክሮ ኢኮኖሚው ያላቸውን አስተዋጾ፣ የተረፈ ምርት አጠቃቀማቸውን መረዳት እንድችሉ /to identify concerned organization/ እና ዩኒቨርሲቲውን ከኢንዱስትሪው ጋር ለማስተሳሰር እንድሁም ዩኒቨርሲቲው የሚያሰለጥናቸው ዜጎች ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃን በማፍራት በፍጥነት ወደ ስራ አለም እንዲገቡ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮምቦልቻ ብረታብረት ፋብሪካ የምርት ክፍል ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ጉርሜሳ ተማሪዎችን ተቀብለው ባስረዱበት ወቅት እንደተናገሩት ‹‹ ስለ ፋብሪካው አጀማመር ታሪካዊ ዳራ፣አሁን ላይ የሚያመርታቸውን ምርቶች፣ ፋብሪካው የሚጠቀማቸውን ጥሬ እዋቀዎች ሙሉ ለሙሉ ከውጭ ሀገር እንደሚያስገባ እና ምርቶቹን ለማምረት የሚያልፉበትን ደረጃ ለተማሪዎች ያስረዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ይህ የብረታ ብረት ፋብሪካ ለሃገር ኢኮኖሚ ያለውን አስተዋጾ በሚገባ እንድረዱ ማድረጉ ምስጋና ይገባዋል›› ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎችም በበኩላቸው በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር ማየታቸውና ከሚመረቁበት ሙያ አንጻር በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን መወሰን እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.