የእቴጌ ጣይቱ የሴት መምህራን ማህበር ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር መግባት ጀመሩ

Research news

በመቅደላ አምባ ኒቨርሲቲ ሴት መምህራን የተቋቋመው ’’ እቴጌ ጣይቱ  የሴት መምህራን ማህበር ” ያዘጋጃቸውን የጥናት ተልሞች  ለውስጥና ለውጭ ገምጋሚዎች አቅርቦ በማስተቸት ማፀደቁ ይታወቃል፡፡

ማህበሩ በዩኒቨርስቲው  ሲቋቋም ሴት ተመራማሪዎች በጥናት ምርምር ፣በማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጅ  ሽግግር  ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ድርሻቸውን እንዲወጡና የአካባበቢውን ሴት የማህበረሰብ ክፍሎች ችግር ለመፍታት  እንድችሉ ብሎም በሀገር ደረጃ ያለውን የሴት ተመራማሪዎች ችግር ለመቅረፍ  ታልሞ መሆኑን የማህበሩ ሰብሳቢ መምህርት ሰዓዳ እንድሪስ ያስረዳሉ፡፡

በማህበሩ 8 የማህበረሰብ አገልግሎት፣ 5 የጥናት ምርምር እንዲሁም 1 የቴክኖሎጂ ሽግግር የጥናት ትልሞች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ወደ ተግባር የገባው የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሴት የቱሉ አውሊያ ከተማና አካባቢ ነዋሪዎችን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡

 የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነችው መምህርት ሶፋኒት ሙሉ ሸዋ እንደገለፀችው ፕሮጀክቱ አራት አይነት የደጋ አፕል ዝርያዎችን ለሀምሳ ሴቶች ለእያንዳንዳቸው አስር በድምሩ አምስት መቶ የአፕል ችግኞችን በማከፋፈልና በማስተከል እንዲሁም ተከታታይነት ያለው ዘላቂ ድጋፍ በመስጠት ችግር ፈች  ስራ ይሰራል፡፡

እንደ መምህርት ሶፋኒት ሙሉ ሸዋ  ገለፃ በፕሮጀክቱ ድጋፍ የተደረግላቸው ሴቶች ቀድመው ስልጠና የወሰዱ ሲሆን የአፕል ችግኞቹን በመንከባከብ ለምርት እንደሚበቋቸው እና አፕል ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ በጤናም በኩል የህፃናት መቀንጨርን እንዲሁም የካንሰር በሽታን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ፡፡

ዶ/ር ካሳሁን አህመድ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት በችግኝ ስርጭቱ ወቅት በቦታው ላይ ተገኝተው ችግኞችን ለሴቶች አስረክበዋል፡፡ይህ የመጀመሪያ ዙር ስራም ውጤታማነቱ ተመዝኖ በቀጣይ ጊዜ የማስፍት ስራ እንደሚሰራ ለኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ ክፍል ሀሳባቸውን ገልፀዋል፡፡    ግንቦት /2012ዓ.ም    

Leave a Reply

Your email address will not be published.