የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በወራሪው የህወሀት ቡድን ለተጎዳው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

Latest News

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የልዑካን ቡድን በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በወራሪው የህወሀት ቡድን የደረሰውን የጉዳት መጠን ተዘዋውሮ በመመልከት ግምቱ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮምፒዩተር፣የፕሪንተርና ወረቀት ድጋፍ አድርጓል፡፡የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የልዑካን ቡድን አስተባባሪ አቶ ከድር ሉጎ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች የሁሉም አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ልጆች የሚማሩባቸው ተቋማት በመሆናቸው ሁላችንም በመተባበር በወራሪው ሃይል የደረሰባቸውን ጉዳት በአካል በማየት መደገፍና ማቋቋም ይገባል ብለዋል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰዋገኝ አስራት በበኩላቸው እንደገለፁት ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለማስጀመር ያግዛል ያለውን በቀዳሚነት ላደረገው ድጋፍና ላሳየው አጋርነት አመስግነው ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማትም ድጋፍ እንድያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ጥር 17/2014 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.