የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ለተጎዳው መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአይነት ድጋፍ አደረገ

Latest News

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህወሀት የሽብር ቡድን አካባቢውን ወሮ በነበረበት ስዓት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉ አውልያ ካምፓስ አጠቃላይ ግምቱ 922520/ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሃያ /ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ድርሻ ደማሜ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ‘’የተደረገው ድጋፍ የጠፋውና የወደመው ሀብት የሁላችንም በመሆኑ በጋራ የመተካት ሃላፊነት ስላለብንና አጋርነትንም ለማጠናከር ያለመ’’ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ድጋፉን የተረከቡት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳሁን አህመድ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ለተደረገው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ በፍጥነት ወደ ስራ እንድንገባ የሚያግዝና ተቋማቶቹ መካከል በጋራ ለመስራት የመደጋገፍ ባህልንም የሚያዳብር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.