የዩኒቨርሲቲው ጥናትናምርምር ዳይሬክተር አገኘ ሽበሽ (ዶ/ር) የ2014 ለ2015 የምርት ዘመን በቱምሳ በተባለ የባቄላ ዝርያና ዳንፌ የስንደ ዝርያዎች የዘር ብዜት ስራ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ተናገሩ ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በቦረና ወረዳ ሀዊ በጣሶ በሚገኘው የምርምር ማዕከል ቱምሳ የሚባል የባቄላ ዝርያ ከኦሮሚያ ምርጥ ዘር በማስመጣት የማላመድ ስራ በመስራት የተሻለ የባቄላ ሰበል እንደተገኘ ተናግርዋል ፡፡ በተመሳሳይ በተንታ ወረዳ በሚገኘው የዛቁናት ምርምር ማዕከል ዳንፌና አጉልቾ የተሰኙ የስንደ ዝርያዎችን በማላመድ የዘር ብዜት ስራው የአይቻልም መንፈስን የስበረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ የሚገኘውን ዘርም ለአከባቢው አርሶ አደር በክላስተር በማደራጀት የማስፋት ስራ እንደሚሰራም አክለው ተናግረዋል ፡፡ያጋገርናቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች እንደተናገሩት በአካባቢው የዚህ አይነት ዝርያ እስካሁን በአካባቢያችን ምርት ይሰጣል የሚል ግምት የለንም ነገር ግን በማዕከሉ የተገኘው ውጤት የአይቻልም መንፈስን የሰበረ መሆኑን በአካል ጎብኝተን የአየን በመሆኑ ዘሩን በግል ማሳችን ለመዝራት አቅደናል ሲሉ ተናግርወል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.